March 6, 2024ቀን 26/06/2016ዓ.ምኦሞ ባንክ ቀደም ሲል ከተለያዩ ክልሎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮዎች ጋር በጋራ ለማከናወን ስምምነት ላይ መድረሱን ተከትሎ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ መዋቅር ጋር በአርባምንጭ ከተማ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ በፋይናንስ እጥረት ምክንያት የዘገዩ የሥራ ዕድል ፈጠራ ግቦችን ለማሳካት ከኦሞ ባንክ ጋር በቅንጅት መስራት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ይገዙ ተናግረዋል። ለወጣቶች ከመነሻ ፋይናንስ እጥረት ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ከኦሞ ባንክ ጋር በተገባው የጋራ ግብ ስምምነት መነሻ ወደ ውጤት ለመቀየርና ኢኮኖሚያቸውን ለማሳደግ ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ተግባር መሆኑን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል። እንደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከባንኩ ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ በተደረሰባቸው አንኳር የሥራ ዕድል ፈጠራና የባንኩ ቅንጅታዊ ስራዎች በሁሉም የዞንና ወረዳ መዋቅሮች ወርዶ በልዩ ክትትል የመረጃ ልውውጥ ተግባራዊ መደረግ እንዳለበት ተናግረዋል። ባንኩ ለሁሉም ህብረተሰብ የፋይናንስ መደላድል በመፍጠር ከኢኮኖሚያዊ ችግር እንዲላቀቁ ከመስራት ሌላ ተልዕኮ እንደሌለው የተናገሩት ደግሞ የኦሞ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አብርሃም አላሮ ናቸው። በቁጠባ ሀብት በማሰባሰብ የብድር ተጠቃሚ ማድረግ የባንኩ ዋንኛው ተግባር መሆኑን ያብራሩት ፕሬዝዳንቱ ባንኩ የህዝብ ገንዘብ አስተዳዳሪ እንደመሆኑ መጠን በተበዳሪዎች እጅ የሚገኝ ገንዘብ ያለመመለስ ዕድል አይኖረውም ብለዋል። ይህንኑ ተመላሽ የገንዘብ ሀብት በማሰባሰብና የወጣቶችን ትክክለኛ ፍላጎት ለይቶ ወደ ስራ ለማስገባት በባንኩና በስራ ዕድል ፈጠራ መዋቅር እንዲሁም ከሌሎች መዋቅሮች ጋር ብርቱ ቅንጅታዊ ስራ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። ይህ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ የዞን አስተዳደርና የፍትህ መዋቅሮች ጋር የተካሄደው የጋራ መድረክ ቀደም ሲል ባንኩ በጋራ ለማካሄድ ባስቀመጠው መርሀ-ግብር መሠረት የተካሄደ ሲሆን የየዞኑ አስተዳደር፣ የክልሉን ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ፍትህ መምሪያዎችንና ፖሊስ ኮሚሽንን ያካተተ መድረክ ነው። ኦሞ ባንክ የሁላችንም ባንክ! [...] Read more...
March 4, 2024ኦሞ ባንክ ከአራቱ ክልሎች ማለትም ከሲዳማ፣ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ከደቡብ ኢትዮጽያ እና ከማዕከላዊ ኢትዮጽያ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በጋራ በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ትርጉም ባለው መልኩ ለመፍታት የሚያስችሉ አገልግሎቶችን ውጤታማ ለማድረግ ከስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮዎች ጋር በጋራ ኃላፊነት በሚወሰዱ ጉዳዮች ተግባብቶ መስራት ወሳኝነት እንዳለው የኦሞ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አብርሃም አላሮ ተናግረዋል፡፡ ባንኩ ለህብረተሰቡ ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ በጋራ ሥራዎች መረጃ ልውውጥ ወቅት ተግዳሮት የሚሆኑ ጉዳዮችን መሠረት ያደረጉ ሥልጠናዎች ተዘጋጅተው ተግባራዊ ይደረጋሉ ብለዋል፡፡ በዚህ መድረክ ተሳታፊ የነበሩ የኦሞ ባንክ ቦርድ አባልና የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀገረጽዮን አበበ በበኩላቸው ባንኩ ከሥራ ዕድል ፈጠራ ካለው ፋይዳ ባሻገር ለመላው ህብረተሰብ ሀብት መፍጠሪያ ባንክ አድርጎ ለመጠቀም እንዲቻል በጋራ ጉዳዮች በቅንጅት መስራት አስፈላጊ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በመድረኩ ተሳታፊ የነበሩ ሁሉም የቢሮ ኃላፊዎች በሰጡት አስተያየት የጋራ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የተፈጠረው የባንኩ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራ ይዝ ቅንጅታዊ አሰራር ወደ ታችኛውም መዋቅር ፈጥኖ መውረድ እንዳለበትና በዚህ መድረክ የጋራ የተደረጉ ስምምነቶችን አክብሮ ተግባራዊ ማድረግ ተገቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ የአራቱም ክልሎች ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊዎች ከባንኩ ፕሬዝዳንት ጋር በ2016 ዓ.ም ቀሪ 5 ወራት ተግባራዊ በሚደረጉ ሥራዎች ዙሪያ የጋራ መግባቢያ ስምምነት ፈጽመዋል፡፡ የጋራ ስምምነቱ በመርሀ-ግብሩ መሠረት ወደ ታችኛው መዋቅር የሚወርድ ሲሆን በባንኩ ዲስትሪክቶችና የኢንተርፕራይዝ መምሪያ፣ በባንኩ ቅርንጫፍ እና ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤቶች አስፈፃሚነት ተሳታፊ አካላቶችን ጨምሮ ተግባራዊ እንደሚሆንም አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ ኦሞ ባንክ የሁላችንም ባንክ! [...] Read more...
December 22, 2023ሀዋሳ: ታህሳስ 11/2016 ዓ.ምኦሞ ባንክ አክሲዮን ማህበር በ2015 ዓ.ም አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን 262 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱንም አስታውቋል::ኦሞ ባንክ አክሲዮን ማህበር 2ኛ መደበኛና አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ አካሂዷል::የአሁኑ ኦሞ ባንክ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ የሚኖሩ ዜጎችን ለማገዝ ዓላማ በማድረግ ከ25 አመት በፊት ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በሚል ስያሜ ነበር የተመሠረተው::በቆይታው የበርካታ ዜጎችን ህይወት የቀየሩ ሥራዎች መከናወናቸውን የኦሞ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አብርሃም አላሮ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል::በመካከለኛና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የነበሩ ዜጎች ደግሞ ሀብታቸውን እዲያሳድጉ አስችሏልም ብለዋል::ከቅርብ አመታት ወዲህ ተቋሙ የብሔራዊ ባንክ መስፈርትን አሟልቶ ወደ ባንክ ደረጃ ያደገ ሲሆን ባላፉት አመታት ባንኩ በተሟላ መልኩ አገልግሎ እንዲሰጥ ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል::በሂደቱ የአደረጃጀት ለውጥ ተደርጓል ብለዋል ፕሬዝዳንቱ:: የማይክሮፋይናንስ ተቋም በነበረ ወቅት የነበረው አደረጃጀት ለባንክ አሰራር አመቺ ባለመሆኑ ነው የአደረጃጀት ለውጥ ያስፈገው ብለዋል:: በ2015 ዓ.ም ኦሞ ባንክ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ 262 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱንም አስታውቀዋል::ኦሞ ባንክ ዛሬ ባካሄደው 2ኛ መደበኛ እና አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤው ዋና መሥሪያ ቤቱ አዲስ አበባ እንዲሆን ተወስኗል::በአሁኑ ሰዓት የኦሞ ባንክ ከ6 ሺ በላይ ሠራተኞች እና ከ250 በላይ ቅርጫፎች አሉት:: ኦሞ ባንክ የሁላችንም ባንክ!! [...] Read more...
July 30, 2023ኦሞ ባንክ (አ.ማ) ከዚህ ቀደም በደ/ብ/ብ/ህ/ክልል ፣ በሲዳማ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቁጠባ፣ የብድር፣ የኢንሹራንስ እና ለሎች አገልግሎቶችን ሲሰጥ የቆየው አንጋፋው ተቋም የአገልግሎት አድማሱን በማስፋፋትና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ በሀገሪቱ መዲና በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ቅርጫፎችን በመክፈት በቅርቡ ሙሉ አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ይገኛል ። ኦሞ ባንክ የሁላችንም ባንክ !! [...] Read more...
July 30, 2023ባንኩን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይበልጥ ለማዘመን በሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፡፡ ባንኩ ከህዋዌ(Huawei) ኢትዮጵያ ጋር በቴክኖሎጂ ትውውቅና አጠቃቃም ዙሪያ የጋራ የምክክር መድረክ አካሄዷል፡፡ በኦሞ ባንክ አይቲ መሠረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መኮንን እንደተናገሩት ባንኩን ለፋይናንስ ኢንዱስትሪ ምቹ በሆኑ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አዘምኖ ስራ ለማስጀመር በሚያስችሉ ጉዳዮች አለም አቀፍ ዕውቅና ካላቸው የቴክኖሎጂ አቅራቢ ድርጅቶች ጋር የተደረገው ውይይት ውጤታማ ነው ብለዋል፡፡ በተለይም በዛሬው ዕለት ከህዋዌ ኢትዮጵያ ጋር የተደረገው ውይይት ዘርፈ ብዙ የቴክኖሎጂ ትውውቅ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።                                                                                                              ኦሞ ባንክ የሁላችንም ባንክ! [...] Read more...