Author Archives: admin

ወጣቶችን የስራ ዕድል ፈጠራ ከፋይናንስ ተጠቃሚነት ጋር አቀናጅቶ በመምራት ኢኮኖሚያቸውን በማሳደጉ ተግባር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

ቀን 26/06/2016ዓ.ምኦሞ ባንክ ቀደም ሲል ከተለያዩ ክልሎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮዎች ጋር በጋራ ለማከናወን ስምምነት ላይ መድረሱን ተከትሎ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ መዋቅር ጋር በአርባምንጭ ከተማ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ በፋይናንስ እጥረት ምክንያት የዘገዩ የሥራ ዕድል ፈጠራ ግቦችን ለማሳካት ከኦሞ ባንክ ጋር በቅንጅት መስራት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል […]

በዝቅተኛና መካከለኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የኢኮኖሚው ተጠቃሚ ለማድረግ የጋራ ኃላፊነት መወጣት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ፡፡

ኦሞ ባንክ ከአራቱ ክልሎች ማለትም ከሲዳማ፣ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ከደቡብ ኢትዮጽያ እና ከማዕከላዊ ኢትዮጽያ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በጋራ በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ትርጉም ባለው መልኩ ለመፍታት የሚያስችሉ አገልግሎቶችን ውጤታማ ለማድረግ ከስራ ዕድል ፈጠራ ቢሮዎች ጋር በጋራ ኃላፊነት በሚወሰዱ ጉዳዮች ተግባብቶ መስራት ወሳኝነት እንዳለው የኦሞ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ […]

ኦሞ ባንክ 262 ሚሊየን ብር ትርፍ አገኘ

ሀዋሳ: ታህሳስ 11/2016 ዓ.ምኦሞ ባንክ አክሲዮን ማህበር በ2015 ዓ.ም አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን 262 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱንም አስታውቋል::ኦሞ ባንክ አክሲዮን ማህበር 2ኛ መደበኛና አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ አካሂዷል::የአሁኑ ኦሞ ባንክ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ የሚኖሩ ዜጎችን ለማገዝ ዓላማ በማድረግ ከ25 አመት በፊት ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በሚል ስያሜ ነበር የተመሠረተው::በቆይታው […]

የፌደራል ክህሎት ሚኒስተር የኢትዮጵያ የአለም ስራ ድርጅት (ILO) አባል የሆነችበትን 100ኛ ዓመት እና ብሔራዊ የስራ ጉባኤ ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀው የዕውቅና ሽልማት ውድድር ምቹ ስራ እንዲፈጠርና የኢንዲስትሪ ግንኙነት እንዲረጋገጥ በማድረግ ኦሞ ባንክ በአገልግሎት ዘርፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆኑ እንኳን ደስ አለን/ አላችሁ!!

ኦሞ ባንክ (አ.ማ) በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ቅርጫፎችን በመክፈት በቅርቡ ሙሉ አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ይገኛል ።

ኦሞ ባንክ (አ.ማ) ከዚህ ቀደም በደ/ብ/ብ/ህ/ክልል ፣ በሲዳማ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቁጠባ፣ የብድር፣ የኢንሹራንስ እና ለሎች አገልግሎቶችን ሲሰጥ የቆየው አንጋፋው ተቋም የአገልግሎት አድማሱን በማስፋፋትና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ በሀገሪቱ መዲና በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ቅርጫፎችን በመክፈት በቅርቡ ሙሉ አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ይገኛል ። ኦሞ ባንክ የሁላችንም ባንክ !!

ባንኩን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይበልጥ ለማዘመን በሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፡፡

ባንኩን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይበልጥ ለማዘመን በሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው፡፡ ባንኩ ከህዋዌ(Huawei) ኢትዮጵያ ጋር በቴክኖሎጂ ትውውቅና አጠቃቃም ዙሪያ የጋራ የምክክር መድረክ አካሄዷል፡፡ በኦሞ ባንክ አይቲ መሠረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መኮንን እንደተናገሩት ባንኩን ለፋይናንስ ኢንዱስትሪ ምቹ በሆኑ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አዘምኖ ስራ ለማስጀመር በሚያስችሉ ጉዳዮች አለም አቀፍ ዕውቅና ካላቸው የቴክኖሎጂ […]

የባንኩ አክሲዮን ሽያጭ ከህብረተሰቡ ጋር የነበረውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠነክር መሆኑ ተገለፀ።

የባንኩ አክሲዮን ሽያጭ ከህብረተሰቡ ጋር የነበረውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠነክር መሆኑ ተገለፀ። በዲላ ከተማ በተደረገው የአክሲዮን ሽያጭ መርሀ-ግብር ከ3.4 ሚሊዮን ብር በላይ ሽያጭ ተካሂዷል። የአክሲዮን ግዢ የፈፀሙ በከተማው የሚኖሩ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደተናገሩት ባንኩ በማይክሮ ፋይናንስ ደረጃ በነበረበት ወቅት የህዝቡ የቅርብ አጋር ሆኖ ሲያገለግል ቆይቶ ወደ ባንክ ተሸጋግሮ በአክሲዮን ባለቤትነት እንድንሳተፍ ይህን ዕድል ይዞ መምጣቱ […]

ኦሞ ባንክ ከአገልግሎቱ ተጠቃሚ ደንበኞች ጋር ያለውን ግንኙነት እንደገና የማደስ እንቅስቃሴውን አጠናክሮቀጥሏል::

ኦሞ ባንክ ከአገልግሎቱ ተጠቃሚ ደንበኞች ጋር ያለውን ግንኙነት እንደገና የማደስ እንቅስቃሴውን አጠናክሮ ቀጥሏል:: መልካም የስራ ግንኙነትና የቁጠባ ሳምንትን ምክንያት በማድረግ በሀዋሳ ዲስትሪክት ስር ከሚገኙ የተለያዩ ቅርንጫፍ ደንበኞች ጋር የምክክር መድረክ አካሄዷል :: ከዲስትሪክቱ የተለያዩ ቅርንጫፎች ጋር በተደረገው የደንበኞች ግንኙነት መድረክ ላይ የተገኙት የሀዋሳ ዲስትሪክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሽመልስ ሽብሩ እንደተናገሩት ባንኩ ማይክሮ ፋይናንስ ከነበረ በት […]