ተቋሙ እያደረገ ያለው የባንክ ሽግግር ለኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና ለማህበራዊ ዕድገት ወሳኝ ድርሻ ያለው መሆኑ ተገለፀ፡፡

በዛሬው ዕለት በባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ የፀደቁ የመመስረቻ ጽሑፍና ቃለ-ጉባኤ የሰነድ አረጋጋጭና መዝጋቢ አካል በተገኙበት የፊርማ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡

ሰኔ 10/2014 ዓ.ም ሀዋሳ

በአሁኑ ጊዜ ወደ ዘመናዊ ባንክ ኢንዱስትሪው ሽግግር እያደረገ ያለው ተቋሙ በፋይናንስ ተደራሽነቱና ካነገበው የረዥም ጊዜ ራዕይ አንፃር አንድ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር የሚያጠናክር፣ በቴክኖሎጂ ተፎካካሪ የፋይናንስ ተቋም እንደሆነ በፊርማ ስነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ኃ/ጊዮርጊስ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ በገበያ ላይ እየመጣ ያለው ዘመናዊ ባንክ በአገልግሎት አሰጣጡና በተሻለ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ሥርዓት ተፎካካሪ ሆኖ መገኘት ጊዜው የሚጠይቅ በመሆኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እየገዛ መሆኑን ተጨማሪ ያደረጉት ዋና ስራ አስፈፃሚው ከአቻ ተቋማት ጋር በጥራትና በብቃት ተወዳዳሪ የአገልግሎት ማዕከል ለማድረግ በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በፊርማ ስነ-ሥርዓት ላይ የተገኙ የቦርድ አባል አቶ ተፈሪ አባተ በዚህ ወቅት እንደገለጹት አሁን ሽግግር ላይ ያለው ባንክ ብሔራዊ ባንክ የሚጠይቃቸውን በርካታ መስፈርቶችን እያሟላ ብዙ ሂደቶችን አልፎ የመጣ በመሆኑ በአለም አቀፍ ንግድ ትስስር ውስጥ በመግባት በአስመጪና ላኪ ደረጃ ለሚንቀሳቀሱ ለንግዱ ማህበረሰብ ትልቅ ዕድል ይዞ የመጣ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ጊዜ የተገኙ የቦርድ አባል ዶክተር ጌትነት በጋሻው በበኩላቸው የባንኩ ዘርፍ በአሁኑ ወቅት በንግዱ ዓለም በአትራፊነታቸው እየታወቁ ባሉበት በአሁኑ ወቅት ተቋሙ እያደረገ ያለው የባንክ ሽግግር ወሳኝ ወቅት ላይ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ዘገባው፡- የተቋሙ ማርኬቲንግ እና ኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ:-

የፈስቡክ ገጻችንን ይውደዱ- ይከታተሉ Omo Micro Finance Institution S.C@OMFIHQ

የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://t.me/OMFIOFFICIAL

ዌብሳይታችንን ይጎበኙ www.omomfi.com

ዩቱብ ቻናላችንን subscribe ያድርጉ

https://youtube.com/channel/UCUNw5LzOv7CWVhTLt6pKShA

ኢሜይል omfi.corporate@gmail.com

Telegram (https://t.me/OMFIOFFICIAL)
OMFI Official
OMO Micro Finance Institution Official