የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ የተቋሙ የ6 ወራት የተግባር አፈጻጸም በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ፡፡

የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ዳይሬክተሮች ቦርድ የተቋሙን የ2013 የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በገመገመበት ወቅት የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ኃ/ጊዮርጊስ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ወቅቶች ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑን ተናግሮ ብድር ማስመለስ አኳያ አሁንም ችግሮች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

የተቋሙ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ ተቋሙ የጀመራቸው ውስጣዊ የሪፎርም ሥራዎች ውጤት እያስገኙ እንደሆኑ ለዚህም ዋና ዋና ተግባራት አፈጻጸም ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የቦርዱ ሰብሳቢ አክለውም ተቋሙ አገልግሎት አሰጣጡን በመሻሻልና ተቋሙን በማዘመን የተገልጋይ እርካታ ማረጋገጥ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸው የቀሪ ወራት ተግባር በርካታ ሀገራዊና ክልላዊ ፕሮግራሞች በሚከናወኑበት ወቅት የሚተገበር በመሆኑ የዕቅድ ክለሳ ተደርጎ አጠቃላይ የተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች በተቋማዊ ተልዕኮ ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት መንቀሳቀስ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ተቋሙ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጣቸውን መመዘኛዎች ለማሳካት በቁጠባ ሞቢላይዜሽን፣ በበድር ስርጭት እና አመላለስ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት አንዳለበት አቶ ጥላሁን ከበደ ተናግረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የውስጥ ቁጥጥር ሥራ በማጠናከር ምዝበራን መከላከልና ህጋዊ እርምጃዎችን በመውሰድ ተቋሙን ከምዝበራ ለመከላከል የተለየ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት የቦርዱ ሰብሳቢ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም የተቋሙ ዳይሬክተሮች ቦርድ በአፈጻጸም ሪፖርትና በቀረቡ ሌሎች አንጀንዳዎች ላይ ውይይት በማድረግ እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ሰብሰባው አጠናቅቋል፡፡

ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
መጋቢት 02/2013 ዓ.ም
ሀዋሣ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *