የባንኩ አክሲዮን ሽያጭ ከህብረተሰቡ ጋር የነበረውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠነክር መሆኑ ተገለፀ።

የባንኩ አክሲዮን ሽያጭ ከህብረተሰቡ ጋር የነበረውን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠነክር መሆኑ ተገለፀ።

በዲላ ከተማ በተደረገው የአክሲዮን ሽያጭ መርሀ-ግብር ከ3.4 ሚሊዮን ብር በላይ ሽያጭ ተካሂዷል።

የአክሲዮን ግዢ የፈፀሙ በከተማው የሚኖሩ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደተናገሩት ባንኩ በማይክሮ ፋይናንስ ደረጃ በነበረበት ወቅት የህዝቡ የቅርብ አጋር ሆኖ ሲያገለግል ቆይቶ ወደ ባንክ ተሸጋግሮ በአክሲዮን ባለቤትነት እንድንሳተፍ ይህን ዕድል ይዞ መምጣቱ ግንኙነታችንን ይበልጥ የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

ባንኩ ለውስን ባለሀብቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ አክስዮን ሽያጭ በመፈፀም የማጠናቀቅ አማራጭ መንገድ እያለው ለተለያዩ ማህበራዊ መሠረቶችና ግለሰቦች ዕድሉን ይዞ መቅረቡ ከማህበራዊ መሠረቶች ጋር አብሮ የማደግ ፍላጎት እንዳለው የሚየሳይ መሆኑን ህብረተሰቡ ተናግረዋል።

በመርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሞ ባንክ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና የሀብት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ግርማ ደጉ በበኩላቸው ይህንን ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ባንኩን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር የማስተሳሰሩና በተግባር የፋይናንስ አገልግሎቶችን በማዘመን ወደ ባንክ ኢንዱስትሪው በመቀላቀል ተወዳዳሪ ማድረግ የሚያስችሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ዙሪያ በገበያ ላይ አለ የሚባለውን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ግዥ ለመፈፀም ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በዲላ ከተማ በተደረገው የአክሲዮን ሽያጭ መርሀ-ግብር የጌዴኦ ዞን ዋና አፈ-ጉባኤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች፣የንግዱ ማህበረሰብ፣ ነባር ደንበኞችና ባለሀብቶች፣ ባለድርሻ አካላት፣ የዲስትሪክት ማኔጅመንት አባላትና ሠራተኞች ተሳትፎ በማድረግ የአክሲዮን ግዢ ፈጽመዋል።

                                                    ኦሞ ባንክ የሁላችንም ባንክ!