ኦሞ ባንክ 262 ሚሊየን ብር ትርፍ አገኘ

ሀዋሳ: ታህሳስ 11/2016 ዓ.ም
ኦሞ ባንክ አክሲዮን ማህበር በ2015 ዓ.ም አንድ ነጥብ አንድ ቢሊየን ብር ገቢ ያገኘ ሲሆን 262 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱንም አስታውቋል::ኦሞ ባንክ አክሲዮን ማህበር 2ኛ መደበኛና አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን በሀዋሳ ከተማ አካሂዷል::የአሁኑ ኦሞ ባንክ በዝቅተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ የሚኖሩ ዜጎችን ለማገዝ ዓላማ በማድረግ ከ25 አመት በፊት ኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በሚል ስያሜ ነበር የተመሠረተው::በቆይታው የበርካታ ዜጎችን ህይወት የቀየሩ ሥራዎች መከናወናቸውን የኦሞ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አብርሃም አላሮ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል::በመካከለኛና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የነበሩ ዜጎች ደግሞ ሀብታቸውን እዲያሳድጉ አስችሏልም ብለዋል::ከቅርብ አመታት ወዲህ ተቋሙ የብሔራዊ ባንክ መስፈርትን አሟልቶ ወደ ባንክ ደረጃ ያደገ ሲሆን ባላፉት አመታት ባንኩ በተሟላ መልኩ አገልግሎ እንዲሰጥ ሲሰራ መቆየቱን አንስተዋል::በሂደቱ የአደረጃጀት ለውጥ ተደርጓል ብለዋል ፕሬዝዳንቱ:: የማይክሮፋይናንስ ተቋም በነበረ ወቅት የነበረው አደረጃጀት ለባንክ አሰራር አመቺ ባለመሆኑ ነው የአደረጃጀት ለውጥ ያስፈገው ብለዋል::

በ2015 ዓ.ም ኦሞ ባንክ አንድ ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የገለፁት ፕሬዝዳንቱ 262 ሚሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱንም አስታውቀዋል::ኦሞ ባንክ ዛሬ ባካሄደው 2ኛ መደበኛ እና አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤው ዋና መሥሪያ ቤቱ አዲስ አበባ እንዲሆን ተወስኗል::በአሁኑ ሰዓት የኦሞ ባንክ ከ6 ሺ በላይ ሠራተኞች እና ከ250 በላይ ቅርጫፎች አሉት::

ኦሞ ባንክ የሁላችንም ባንክ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *